#ዶ/ር አምሣሉ አክሊሉ ኢትዮጵያ የቋንቋ እና የሥነ-ጽሑፍ ብሎም የታሪክ ቀዳማይ ምሁሮቿን ስትጠቅስ ከፊት ከሚሰለፉት ውስጥ አንዱ ናቸው። ላለፉት ሃምሳ ዓመታት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቅፅር ግቢ ውስጥ በማስተማር እና ከቤተ-መፅሐፍት ውስጥ ባለመጥፋት ይታወቃሉ። ለመሆኑ የዶ/ር አምሣሉ አክሊሉ ሥነ-ጽሑፋዊ እና ሥነ-ልሣናዊ አበርክቶዎች ምንድን ናቸው የሚለውን ሃሣብ በአጭሩ እንቃኘዋለን።
#በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ እስካሁን ድረስ ማስተማሪያ የሆነ የጥናትና የምርምር መፅሐፍ አላቸው። መፅሐፉ ባይታተምም እየተባዛ በየቤተ-መፃሕፍቱ እና በየመምህራኑ እንዲሁም በየተማሪው እጅ ይገኛል። ይህ ጥናትና ምርምራቸው “አጭር የኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ” ይሰኛል። ይህን መፅሐፍ በማንበብ ብቻ ዶ/ር አምሣሉ አክሊሉ ያበረከቱትን ግዙፍ አስተዋፅኦ መናገር ይቻላል።
“አጭር የኢትዮጵያ የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ” የተባለው የዶ/ር አምሣሉ ጥናትና ምርምር እንደ ስሙ አጭር አይደለም። በጣም ብዙ ነው። ከ350 ገጾች በላይ ነው። በውስጡ የያዘው ርዕሰ ጉዳይ ደግሞ ሥነ-ጽሑፍ ብቻም አይደለም። ውስጡ ያለችው ኢትዮጵያ ናት። የኢትዮጵያን ታሪክ እና ሥነ-ጽሑፎቿን ከማስተዋወቁም በላይ የኢትዮጵያ ፀሐፊዎች እነማን እንደነበሩ እና እንደሆኑ ከመጀመሪያው ጀምሮ እስከ 1966 ዓ.ም ድረስ ይተነትናል።
“ፋኖ ተሰማራ
ፋኖ ተሰማራ
እንደ ሆቺ ሜኒ
እንደ ቼኩ ቬራ”
#እያለ ትውልድ በየጐዳናው እየተመመ እስከሚወጣበት ጊዜ ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ቀለል ባለ እና ለማንበብ በማይጐረብጥ ተወዳጅ አማርኛ ፅፈው አስነብበውናል አስተምረውናል።
#ዶ/ር አምሣሉ አክሊሉ ይህን የኢትዮጵያን የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ለመፃፍ ሲነሱ ጅማሮ ያደረጉት የሰው ልጅ አፈጣጠርን ነው። ገና የሰው ልጅ ከየት እንደተፈጠረ፣ የቋንቋ አፈጣጠር እንዴት እንደሆነ፣ የሴሜቲክ እና የኩሽ ሕዝቦች ከየት እንደፈለሱ፣ የት ቦታ እንደተገናኙ፣ ከዚያም ቋንቋዎች እንዴት እንደተፈጠሩ እያስረዳ ይጀምራል። ከዚያም ኢትዮጵያ የምትባለውን ሀገር መጀመሪያ ላይ የፈጠሯት ሕዝቦች እነማን እንደሆኑ መፅሐፋቸው ያስረዳል።
#እነዚህ ሕዝቦች በኋላም ሥርዓተ-መንግሥት መስርተው አክሱም ከተማ ላይ መናኘት እንደጀመሩ ይገልፃሉ። ጽሕፈት የጀመረበትንም ዘመን ያስታውሳሉ። ድንጋይ ላይ የተቀረፁትን ጥንታዊ ጽሁፎችን እና ቅርጾችን እየተነተኑ የመጀመሪያዎቹ ኢትዮጵያዊያን ምን ብለው እንደፃፉ ይነግሩናል። ጀርመናዊው ኢኖ ሊትማን በ1906 ዓ.ም ወደ አክሱም ከተማ መጥተው የተመራመሩበትን የጀርመንኛ ጥናት ወደ አማርኛ ተርጉመው የራሳቸውን መላምትም እየሰጡ ዶ/ር አምሳሉ ኢትዮጵያን አስተምረውናል።
#የድንጋይ ላይ ጽሁፎቹን ዘርዝረው ኢትዮጵያ አፈጣጠሯ እና መሪዎቿ እነ እከሌ ናቸው ካሉን በኋላ ልዩ ልዩ ማኅበረሰባዊ ሽግግሮችን ያሳዩናል። አበሻ የሚለው ቃል ከየት እንደመጣና አበሾች እንዴት እንደሆኑ ያስረዱናል። ቀጥሎም ደግሞ የሴምና የኩሽ ቋንቋዎች በኢትዮጵያ ምድር ጅማሮአቸውና ሥርጭታቸውንም ይተነትናሉ። እንዲህ እያሉ ወደ ሃይማኖት ይገባሉ። የአማርኛ ቋንቋ እንዴት እንደተጀመረና እያደገ እንደመጣ ዶ/ር አምሳሉ ይተነትናሉ።
#ዶ/ር አምሣሉ ኢትዮጵያ ውስጥ ሃይማኖት እንዴት እንደተጀመረ እና እንደተስፋፋ ሥነ-ጽሑፋዊ ማስረጃ እያጣቀሱ ያስተምሩናል። የጥንቆላ ሥነ-ጽሁፎችን ሁሉ እያቀረቡ ይተነትናሉ። ቀጥሎም ወደ ቤተ-ክሕነት ውስጥ ይገቡና የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስትያን ለሥነ-ጽሑፍ ማደግ እና መጐልበት ያበረከተችውን አስተዋፅኦ ዝርዝር አድርገው ፅፈዋል።
#ቤተ-ክርስትያን ውስጥ በብፁ አበዎች የተፃፉ ገድሎችን እና የእምነት መፃሕፍቶችን እየጠቃቀሱ ሥነ-ፅሁፋዊ ፋይዳቸውን ይገልፃሉ። የኢትዮጵያ ሃይማኖታዊ ሥነ-ፅሁፎችን ጠለቅ ብሎ በመመርመር ዶ/ር አምሣሉ አክሊሉ ከፍተኛውን አስተዋፅኦ አበርክተዋል። ምናልባት የመጀመሪያ ድግሪያቸውም ከካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ተምረው መመረቃቸውም ዘርፉን ጠንቅቀው እንዲያውቁት ሳያደርጋቸው አልቀረም። በኋላም እዚያው ካይሮ ውስጥ ከሚገኘው የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲ በ1949 ዓ.ም በባችለር ኦፍ አርት ዲግሪ ተመርቀዋል።
#ዶ/ር አምሣሉ በዚሁ የኢትዮጵያን ሥነ-ጽሑፍ በሚቃኘው ጥናታቸው ውስጥ ታላላቅ ኢትዮጵያዊያንንም እያነሳሱ ያጫውቱናል። ገና ዓለም ሀ ብሎ በሚነቃበት ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ እነማን በፅሁፍ ጥበብ ይራቀቁ እንደነበር ያስታውሱናል። እንዲህ እያሉ በየዘመኑ የተነሱትን የቋንቋ እና የሥነ-ጽሑፍ ታሪኮችን እያወሱ 14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ያለውን የኢትዮጵያን ገናና ንጉስ አፄ ዘርአያዕቆብን ይጠቅሳሉ።
#አፄ ዘርአያዕቆብ አስገራሚ ንጉሥ ነበር። ደራሲ ነው። በርካታ መፃህፍትን ደርሷል። ሃይማኖት ኢትዮጵያ ውስጥ መሠረቱን እንዳይለቅ በደንብ አድርጐ መሠረቱን የተከለ ንጉስ እንደነበር ዶ/ር አምሣሉ ያስረዱናል።
#ኢትዮጵያዊያን ጥንታዊ ፀሐፊዎች በዓለም ዙሪያ የተፃፉ ታላላቅ ፅሁፎችን ወደ ሀገርኛ በመመለስ እና ሀገርኛ ወዝና ለዛ በመስጠት ይፅፏቸው እንደነበር እየዘረዘሩ ፅፈዋል።
እንዲህ እያለ የዶ/ር አምሣሉ ጥናት 17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ይደርሣል። 17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ጉዳዮች የተከሰቱበት ነበር። ምክንያቱም በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ላይ ከምስራቅ ኢትዮጵያ የተነሳው ጦረኛው ግራኝ ባስነሳው አመፅ ብዙ ችግር ተከስቶ ነበር። ከዚያም የኢትዮጵያን ማዕከላዊ መንግሥት ለመርዳት ፖርቺጊዞች እና እስፓኒያርዶች ወደ ኢትዮጵያ ገብተው ከመቶ ዓመታት በላይ ጐንደር ውስጥ ተቀመጡ።
#ከዚያም የራሳቸውን ሃይማኖት ማስፋፋት ጀመሩ። ከ1624 ዓ.ም በፊት ኢትዮጵያን ሲመሩ የነበሩትን አፄ ሱስኒዮስን ሃይማኖታቸውን አስቀየሯቸው። ኢትዮጵያም ወደ ብጥብጥ ገባች። ወደ ስምንት ሺ ህዝብ አለቀ። አፄ ፋሲልም ወደ ስልጣን መጡ። ፋሲልም ሰባት ሺ ፈረንጆችን ከኢትዮጵያ አስወጡ። የቀድሞውን ሃይማኖት መልሰው አመጡ። ወደ ስልጣኔም መንገድ ተጓዙ። ታዲያ የዚያን ጊዜ አንድ ፈላስፋ ኢትዮጵያ ውስጥ ብቅ አለ። ዘርአያዕቆብ ይባላል። አክሱም ውስጥ ተወልዶ ጐንደር የኖረ ነው። ዶ/ር አምሳሊ የዚህን ፈላስፋ ፅሁፍ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የሚነገሩትን ነገሮችን በዝርዝር ያሳዩን ናቸው። ዘርአያዕቆብ ኢትዮጵያዊ አይደለም፤ ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት ፈላስፋ ሊኖራት አይችልም ብለው ዜግነቱን ከኢትዮጵያ ላይ የነጠቁትን ጣሊያናዊውን ኮንቲ ሮሲኒንን በተባ ብዕር ዶ/ር አምሳሉ ተከራክረዋቸዋል። ዘርአያዕቆብ ኢትዮጰያዊ እንደሆነ በርካታ ማስረጃዎችን እየጠቀሱ አስተምረዋል።
#የዶ/ር አምሣሉ ጥናት እንዲህ እያለ እስከ 1900 ዓ.ም ላይ ይደርሳል። በዚህ ዓመት ላይ አንድ አዲስ ልቦለድ መፃፉን ይነግሩናል። የነጋድራስ አፈወርቅ ገ/እየሱስ ጦቢያ የተሰኘችው ልቦለድ ታሪክ የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ የልቦለድ መፅሐፍ መሆኗን እየተነተኑ ያስረዱናል። ደራሲዋ ነጋድራስ /ፕሮፌሰር/ አፈወርቅ ገ/እየሱስ ማን እንደሆኑ እና ታሪካቸውንም ማውሳት ይጀምራሉ።
#የኢትዮጵያን ታላላቅ ደራሲያን በየዘመኑ እና በየስርዓቱ እየከፋፈሉ ታሪካቸውን እና ስራዎቻቸውን ጽፈዋል። የነ ገብረህይወት ባይከዳኝን፣ የነ ብላቴን ጌታ ኅሩይ ወ/ስላሴን፣ የነ መኰንን ሀብተወልድን፣ የነ ሐዲስ አለማየሁን፣ የቀኝ ጌታ ዮፍታሄ ንጉሴን፣ የነ ደጃዝማች ግርማቸው ተ/ሃዋርያትን፣ የነ ተክለሐዋርያት ተ/ማርያምን እና የመሳሰሉትን ቀደምት ደራሲያን ስራዎችና ታሪኮች በሚገባ ፅፈው አስተላልፈዋል ዶ/ር አምሣሉ።
#ከዚያም በመለጠቅ የመጡትን ነበልባል ትውልዶች ታሪክና ስራዎች ይዘክራሉ። እነ ፀጋዬ ገ/መድህን፣ አቤ ጉበኛ፣ ብርሃኑ ዘሪሁን፣ ዳኛቸው ወርቁ፣ ዮሐንስ አድማሱ፣ ኃይሉ ገ/ዮሐንስ /ገሞራው/፣ አበበ ወርቄ፣ ይልማ ከበደ፣ ኢብሳ ጉተማ፣ የመሳሰሉ የዘመኑ አንፀባራቂ ደራሲዎችን እና ገጣሚዎች ስራዎችን እየተነተኑ የፃፉልን ታላቅ ባለውለታችን ናቸው።
#ይህ አጭር የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሑፍ ታሪክ የተሰኘው የዶ/ር አምሣሉ ጥናት ታሪኩን ገና ከፍጥረተ-ዓለም ይጀምርና የሚያቆመው ደርግ “ትሪሪም ትሪሪም” እያለ እስከሚመጣበት ወቅት ድረስ ነው። ታዲያ እስከዚያው ዘመን ድረስ ያለውን ታሪክ በሚገባ የፃፉልን ሰው በመሆናቸው ለዘለዓለም ስናስታውሳቸው እንኖራለን።
#ዶ/ር አምሣሉ የሰሯቸው ስራዎች በርካታ ናቸው። ለምሳሌ ከእያንዳንዱ ተማሪ እጅ የማይጠፋውን “እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት” ከጂ.ፒ ሞስባክ ጋር በመሆን በ1966 ዓ.ም አሳትመዋል። ስለዚሁ መዝገበ ቃላት የዛሬ ዓመት ግድም ለጋዜጠኛ ቢኒያም ከበደ ዶ/ር አምሣሉ አጫውተውት ነበር። መዝገበ ቃላቱ አስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ሁለት ሚሊዮን ኮፒ ታትሞ ተሰራጭቷል። ይህ የሕተመት ቁጥር እጅግ ብዙ እንደሆነም ይነገራል።
#ከዚህ በተጨማሪም ከደራሲ ዳኛቸው ወርቁ ጋር በመሆን “የአማርኛ ፈሊጣዊ አነጋገሮች” የተሰኘ መፅሐፍ አሳትመዋል። ከደምሴ ማናህሎት ጋር ሆነው ደግሞ “ጥሩ የአማርኛ ድርሰት እንዴት ያለ ነው?” የሚል መፅሐፍ አላቸው። “የአማርኛ ሞክሼ ሆሄያት ጠንቅቆ ያለመፃፍ ችግርና መፍትሄ” የተሰኙ መፃሐፍትን ከማሳተማቸው ሌላ የአማርኛ አረብኛ መዝገበ ቃላትና ሌሎች የጥናትና ምርምር መፃህፍትን አሳትመዋል።
#በ1922 ዓ.ም ደሴ ከተማ የተወለዱት ዶ/ር አምሣሉ አክሊሉ የዶክትሬት ድግሪያቸውን በ1954 ዓ.ም ከጀርመን ሀገር ቱቢንግ ዩኒቨርሲቲ የተቀበሉ ቀዳማይ ምሁር ናቸው።
ዶ/ር አምሣሉ አክሊሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለብዙ ዓመታት ቋንቋና ሥነ-ጽሑፍን አስተምረዋል። ከ1955-1985።
#ከዚያም በኋላ ቢሆን ከዩኒቨርሲቲው ውስጥ የማይጠፉ እና እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ጥናትና ምርምር የሚያደርጉ ነበሩ። ታህሳስ 10 ቀን 2006 ዓ.ም እኚህ ትላቅ ምሁር በ84 ዓመታቸው አረፉ። ታህሳስ 13 ቀን 2006 ዓ.ም በየካ ሚካኤል ቤተ-ክርስትያን ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ጓደኞቻቸውና ተማሪዎቻቸው በተገኙበት ሥነ-ሥርዓት ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል።
©ጥበቡ በለጠ
Dr. Amsalu Aklilu
Ethiopian Linguist and Literary Scholar (1929 – 2013)
Dr. Amsalu Aklilu stands among Ethiopia’s foremost scholars in language, literature, and history. For the past fifty years, he was a constant presence, teaching within the compounds of Addis Ababa University and always found in its libraries. Let’s briefly explore Dr. Amsalu Aklilu’s literary and linguistic contributions.
He has a research and study book that is still used as a teaching material at Addis Ababa University. Although the book is unpublished, it’s widely duplicated and found in libraries, in the hands of teachers, and among students. This study and research is titled “A Short History of Ethiopian Literature.” Simply by reading this book, one can grasp the immense contribution Dr. Amsalu Aklilu made.
“A Short History of Ethiopian Literature,” Dr. Amsalu’s study and research, is not short as its name suggests. It is quite extensive, exceeding 350 pages. The subject matter it covers is not limited to literature alone; within it lies Ethiopia itself. Beyond introducing Ethiopian history and its literatures, it analyzes who Ethiopian writers were and are, from the very beginning up to 1974 G.C.
He taught us and made us read about the history of Ethiopian literature in a simple, readable, and beloved Amharic, even up to the time when generations rallied in the streets singing:
“Fano Tesemara, Fano Tesemara Like Ho Chi Minh Like Che Guevara“
When Dr. Amsalu Aklilu set out to write this history of Ethiopian literature, he began with the creation of humankind. He starts by explaining where humans originated, how language was created, where Semitic and Cushitic peoples migrated from, where they met, and then how languages were formed. His book then explains who were the first people to establish the country called Ethiopia.
He describes how these peoples later established a system of government and began to rule in the city of Axum. He recalls the era when writing began. Analyzing ancient inscriptions and carvings on stones, he tells us what the first Ethiopians wrote. Dr. Amsalu educated us about Ethiopia by translating German research by the German scholar Enno Littmann, who came to Axum in 1906 Ethiopian calendar. to conduct research, while also offering his own hypotheses.
After listing the stone inscriptions and telling us about Ethiopia’s formation and its leaders, he shows us various societal transitions. He explains where the word “Abesha” came from and how the Abesha people came to be. Subsequently, he analyzes the origins and spread of Semitic and Cushitic languages on Ethiopian soil. Proceeding in this manner, he delves into religion. Dr. Amsalu analyzes how the Amharic language began and developed.
Dr. Amsalu teaches us how religion began and spread in Ethiopia, citing literary evidence. He presents and analyzes even the literature of divination. Next, he delves into the church and meticulously writes about the Ethiopian Orthodox Church’s contribution to the growth and development of literature.
Citing hagiographies written by blessed fathers within the church and other religious texts, he explains their literary significance. Dr. Amsalu Aklilu made a significant contribution by thoroughly examining Ethiopian religious literature. Perhaps his first degree in religious studies from Cairo University also played a role in his profound understanding of the field. Later, in 1957 G.C., he graduated with a Bachelor of Arts degree from the American University in Cairo.
In this study of Ethiopian literature, Dr. Amsalu also engages us by highlighting great Ethiopians. He reminds us who excelled in the art of writing in Ethiopia when the world was just beginning to awaken. Recalling the history of language and literature from various eras, he mentions the renowned Ethiopian Emperor Zara Yaqob from the 14th century.
Emperor Zara Yaqob was an amazing king. He was an author who wrote numerous books. Dr. Amsalu explains that Zara Yaqob was a king who firmly established the foundation of religion in Ethiopia so that it would not be lost.
He wrote by detailing how ancient Ethiopian writers translated great texts written around the world into local languages, imbuing them with local flavor and charm.
Dr. Amsalu’s study then reaches the 17th century. This century saw many events unfold in Ethiopia. This was because much trouble arose from the rebellion stirred by Gragn, the warrior who emerged from eastern Ethiopia in the 16th century. Then, to assist the central Ethiopian government, Portuguese and Spaniards entered Ethiopia and remained in Gondar for over a hundred years.
They then began to spread their own religion. They changed the religion of Emperor Susenyos, who had been ruling Ethiopia before 1632 G.C. Ethiopia plunged into turmoil, and about eight thousand people perished. Emperor Fasil then came to power. Fasil expelled seven thousand foreigners from Ethiopia. He restored the former religion and embarked on a path towards civilization. It was then that a philosopher emerged in Ethiopia, named Zara Yaqob, born in Axum and lived in Gondar. Dr. Amsalu meticulously shows us this philosopher’s writings and the narratives associated with him. Dr. Amsalu ably debated the Italian Conti Rossini, who stripped Zara Yaqob of his Ethiopian nationality, claiming he was not Ethiopian and that Ethiopia could not have such a philosopher. Dr. Amsalu taught by citing numerous pieces of evidence that Zara Yaqob was indeed Ethiopian.
Dr. Amsalu’s study continues until it reaches 1908 G.C. In this year, he tells us about the writing of a new novel. He analyzes and explains that Negadras Afework Gebreyesus’s novel “Tobia” is Ethiopia’s first novel. He then begins to discuss who the author, Negadras/Professor Afework Gebreyesus, was and his history.
He wrote about the history and works of great Ethiopian authors, categorizing them by era and system. Dr. Amsalu extensively wrote and transmitted the works and histories of early authors such as Gebrehiwot Baykedagn, Blatten Geta Hiruy Wolde Selassie, Mekonnen Habtewold, Haddis Alemayehu, Qegn Geta Yoftahe Nigussie, Dejazmach Girmachew Tekle Hawaryat, Tekle Hawaryat Tekle Mariam, and others.
He then recounts the history and works of the subsequent generations of vibrant writers, including Tsegaye Gebre-Medhin, Abe Gubegna, Birhanu Zerihun, Dagnachew Worku, Yohannes Admasu, Hailu Gebre-Yohannes (Gemora), Abebe Worke, Yilma Kebede, Ibsa Gutema, and other brilliant contemporary authors and poets, analyzing their works, for which we owe him a great debt.
This study by Dr. Amsalu, titled “A Short History of Ethiopian Literature,” begins its historical narrative from the creation of the world and concludes with the advent of the Derg regime. As he is the person who meticulously wrote the history up to that era, we will remember him forever.
Dr. Amsalu’s works are numerous. For instance, in 1974 G.C., he co-published the “English-Amharic Dictionary” with G.P. Mosback, a dictionary that is indispensable for every student. About a year ago, Dr. Amsalu shared some insights about this dictionary with journalist Biniyam Kebede. Up until recently, two million copies of the dictionary have been printed and distributed, a print number reportedly considered very large.
In addition, he co-authored “Amharic Idiomatic Expressions” with author Dagnachew Worku. With Demse Manahlot, he also has a book titled “What Makes a Good Amharic Composition?” Besides publishing books such as “The Problem of Not Mastering Amharic Homophonous Letters and Its Solution,” he also published an Amharic-Arabic dictionary and other research and study books.
Born in Dessie in 1929 G.C., Dr. Amsalu Aklilu was a pioneering scholar who received his doctorate in 1962 G.C. from the University of Tübingen in Germany.
Dr. Amsalu Aklilu taught language and literature at Addis Ababa University for many years, from 1963 to 1993 G.C.
Even after that, he remained a constant presence at the university, conducting research and studies until recently. On December 19, 2013 G.C., this great scholar passed away at the age of 84. On December 20, 2013 G.C., his funeral ceremony was held at Yeka Mikael Church, attended by his relatives, friends, and students.
© Tibebe Belete
References
Ethiopian History and Tourism/የኢትዮጵያ ታሪክና ቱሪዝም
Facebook Channel. https://shorturl.at/1Gwmt
