ሎካላይዝ የሚደረገውን ሶፍትዌር ማዘጋጀት – ክፍል 3
ሎካላይዜሽን ጠቃሚ ያልሆነ እና ብዙ ጊዜ የሚፈጅ ነገር ተደርጎ ይወሰዳል፣ በዚህም ምክንያት ብዙ ድርጅቶች ጊዜው እስኪረፍድ ድረስ ለጉዳዩ ቦታ አይሰጡትም። ሶፍትዌር አዘጋጆቹ ኮዱን ሲያዘጋጁ ለሌሎች ቋንቋዎች፣ ዓለም አቀፋዊ ቅርጾች ወይም ሌሎች አስፈላጊ የሎካላይዜሽን ክፍሎች ትኩረት ባለመስጠታቸው ምክንያት ወደፊት ሌሎች ቋንቋዎችን ለማካተት ሙሉ ፕሮጀትዎትን እንደገና ማስተካከል ሊኖርብዎት ይችላል። ነገሮች ተበላሽተው ወደ ውድቀት ለማምራት ትንሽ ስሕተት በቂ ነው። በመነሻ ይዘቱ ላይ ያሉ ስህተቶች ቀድመው በአግባቡ ካልተስተካከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ሊደገሙ ብሎም የበለጠ ጎልተው ሊቀርቡ ይችላሉ። ከትርጉም በኋላ የሎካላይዜሽን ስህትቶችን በማረም ወራትን ማባከን ካልፈለጉ፣ ከመጀመሪያው ሶፍትዌርዎትን ዓለም አቀፋዊ ያድርጉ። ይህም ማለት በቀላሉ እና በመጠነኛ…